የሚቀረፁ አጀንዳዎች የሴቶችን ጥያቄ ያካተቱ መሆን እንዳለባቸው በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከጥምረት ለሴቶች ድምፅ ጽሕፈት ቤት ተሳታፊ የሆኑት እየሩሳሌም ሰለሞን ተናገሩ።የማህበሩ ዋና ዓላማ ሴቶች በበቂ ሁኔታ በምክክሩ እንዲሳተፉ ማድረግ መሆኑንም ነው የገለፁት።ሴቶች በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች በተለይም በፖለቲካው በበቂ ሁኔታ እና ቁጥር እንዲሳተፉ የተመቻቹ ሁኔታዎች አናሳ መሆናቸውንም ተናግረዋል።ተቋሙ በተለያዩ ክልሎች ያሉ ሴቶች ወደ ጠረጴዛ እንዲመጡ ማድረግ ቀዳሚ ስራው እንደሆነ እየሩሳሌም ተናግረዋል።
EBC
More Stories
ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ለምክር ቤቱ ማብራሪያ ይሰጣሉ
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ኢትዮጵያና ዑጋንዳ በቀጣናው ሰላምና ፀጥታን በማስፈን ረገድ ጉልህ ሚና አላቸው አሉ
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በኮምቦልቻ ከተማ ተጀመረ