የፅዱ ኢትዮጵያ ክልላዊ መረሃ ግብር ማስጀመሪያ ንቅናቄ መድረክ በታርጫ ከተማ እየተካሄደ ነዉ ።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አነሳሽነት እንደ ሀገር የተጀመረው ፅዱ ኢትዮጵያ መረሃ ግብር መነሻ በማድረግ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ንቅናቄው በይፋ ተጀምሯል።
በመድረኩ ላይ ተገኝተዉ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ፅዱ እና ለጤና ተስማሚ የሚሆን አካባቢ መፍጠር ይገባል ብለዋል።
ፅዱ አካባቢ ለመፍጠር ከተማ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ቦታዎች መሠራት እንዳለበትና ከግል ንፅህና ጀምሮ መተግበር እንዳለበት ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የአረንጓዴ ልማትና ውበት ሥራ ሁሉም ተቋማት ድርሻውን እንድወጡና ቆሻሻን የማስወገድ ባህል ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ አሳስበዋል።
የከተሞች ኮርደር ሥራዎች ትኩረት ተደርጎ መሠራት አለበት ያሉ የክልሉ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር የማታለም ቸኮል ያስረዱ ስሆን በክልላችን ያሉ የማዘጋጃ ከተሞች የቱሪስት ስበት ማዕከል እንዲሆንና የሥራ ዕድልም መፍጠር እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ በሽታን መከላከል እንዳለብንና ሁሉም ህብረተሰብ ክፍል የግሉን የአከባቢውን ንፅህና መጠበቅፅዱ ኢትዮጵያን በመፍጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ድርሻቸውን እንድወጡ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵ ህዝቦች ክልል የጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም አስረድተዋል።
ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የፅዱ ኢትዮጵያ ክልላዊ መርሃግብር በታርጫ ከተማ አስጀምረዋል ሲል የዘገበው የክልሉ መ/ኮ/ጉ ብር ነው።
More Stories
የቴፒ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የከተሞች ፕላን ኢኒስቲትዩት ተገለጸ፡፡
የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተመረጡ የግብርና፣ በቱሪዝም፣ በቴክኖሎጂ እና ማዕድን ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበየቻይናዋ ግዛት ከፍተኛ ልዑካን የተሳተፉበት የቻይና-አፍሪካ (ኢትዮጵያ) የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝም ና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በዓለም ለ45ኛ በኢትዮጵያ ለ37ኛ በክልሉ ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረዉ የዓለም የቱሪዝም ቀን ”ቱሪዝም ለሰላም” በሚል መር ቃል በቦንጋ ከተማ እየተከበረ ነዉ።