77ኛው የዓለም ጤና ጉባዔ በስዊዘርላንድ ጀኔቫ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል፡፡“ሁሉም ለጤና፣ ጤና ለሁሉም” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ በሚገኘው ጉባዔ ላይ ከ190 በላይ አባል ሀገራት ተወካዮችና ሌሎች አካላት ተሳትፈዋል፡፡በጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክም በጉባዔው ላይ እየተሳተፈ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡በተለያዩ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳዎች ላይ የሚመክረው ጉባዔው እስከ ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተጠቁሟል፡፡
FBC
More Stories
ኢትዮጵያ የፊታችን ነሀሴ በአንካራ በሚካሄደው ድርድር ምን ትጠብቃለች?
የአይቻልም እና የአይሆንም መንፈስን መስበር ከተቻለ የማይቻል ነገር የለም “- ተማሪ ወጋየሁ ወራጆ
ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ለምክር ቤቱ ማብራሪያ ይሰጣሉ