ሞስኮ የነዳጅ ማደያውን ለመገንባት ያሰበችው በሱዳን ነው ተብሏል
የሱዳን ወታደራዊ መንግስት ለሩሲያ ጥያቄ አወንታዊ ምላሽ መስጠቱ ተገልጿል
ሩሲያ በቀይ ባህር የነዳጅ ማደያ ለመገንባት ጥያቄ ማቅረቧ ተገለጸ፡፡
በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለችው ጎረቤት ሀገር ሱዳን ሩሲያ በቀይ ባህር የነዳጅ ማደያ እንትገነባ ጥያቄ እንደቀረበላት አስታውቃለች፡፡
በሱዳን ጦር ውስጥ አመራር የሆኑት ጀነራል ሰር አል አታ እንዳሉት ሱዳን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ለማግኘት በሚል ከሩሲያ የቀረበላትን ጥያቄ እንደምትቀበል ተናግረዋል፡፡
ሁለቱ ሀገራት ይህን ስምምነት በቀርቡ ሊፈራረሙ እንደሚችሉ አል አረቢያ ጀነራል ያሰር አል አታን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡
ሩሲያ እስካሁን በሱዳን ጦር አመራር ይፋ ስለተደረገው የቀይ ባህር ነዳጅ ማደያ ግንባታ ዙሪያ በይፋ ያለችው ነገር የለም፡፡
ሩሲያ በቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር አስተዳድር ጊዜ በፖርት ሱዳን ወታደራዊ ማዘዣ ለመገንባት ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር፡፡
ፕሬዝዳንቱ በመፈንቅለ ስልጣን ከተወገዱ በኋላ ይህ ስምምነት ሳይተገበር እስካሁን የቆየ ሲሆን የሱዳን ወታደራዊ መንግስት ስምምነቱን እየገመገመ መሆኑን በተደጋጋሚ አስታውቋል፡፡
Al-Ain
More Stories
የጋዛው ጦርነት የሚቆም ከሆነ ሄዝቦላ በእስራኤል ላይ ጥቃት መሰንዘሩን እንደሚያቆም አስታወቀ
የሀውቲ ታጣቂዎች በእስራኤሏ ሀይፋ ወሳኝ ኢላማ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ገለጹ
በህንድ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓት ላይ በተፈጠረ መተፋፈግ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 121 ደረሰ