በሶስት ዙር በረራ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 183 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።
በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱት ዜጎች መካከል ሴቶች እና ጨቅላ ህፃናትም ይገኙበታል።
ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡
ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እስካሁን ከ29 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።
FBC
More Stories
ኢትዮጵያ የፊታችን ነሀሴ በአንካራ በሚካሄደው ድርድር ምን ትጠብቃለች?
የአይቻልም እና የአይሆንም መንፈስን መስበር ከተቻለ የማይቻል ነገር የለም “- ተማሪ ወጋየሁ ወራጆ
ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ለምክር ቤቱ ማብራሪያ ይሰጣሉ