በእነዚህ በሽታዎች በአለም አቀፍ ደረጃ ከ2 ሚልየን በላይ ሰዎች ህይወት እያለፈ መሆንን የአለም ጤና ድርጅት አስታውቋል
ከፍተኛ ስርጭት አለባቸው የሚባሉ ሀገራት በ2030 የበሽታውን ስርጭት በ10 እጥፍ ለመቀነስ ዕቅድ ይዘው ነበርየአለም ድርጅት አዲስ ያወጣው ሪፖርት በብዙዎች ዘንድ ችላ የተባለው ኤቺ አይቪ ኤድስ እና ሌሎች በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለለፉ በሽታዎች በአመት 2.5 ሚልየን ዜጎችን ህይወት እየቀጠፉ መሆናቸውን አመላክቷል፡፡ድርጅቱ በተለይ በአሜሪካ እና አፍሪካ የሚገኝውን ከፍ ያለ የበሽታውን ስርጭት ከ7.8 ሚልየን ወደ 0.7ሚልየን ለመቀነስ እቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።ይሁንና በ2022 ከ15-49 እድሜ ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ላይ አንድ ሚልዮን አዲስ ኢንፌክሽን ተመዝግቧል፡፡የድርጅቱ ዋና ኃላፊ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም ባለፉት አመታት በኤድስ ላይ የተደረገው ዘመቻ የሚታይ ለውጥ የተመዘገበበት ቢሆንም አሁን ላይ ከግብረስጋ ግንኙነት ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ በሽታዎች ቁጥር መጨመር ቫይረሱ ዳግም እንዳያንሰራራ የሚያሰጋ ነው ብለዋል፡፡በተለይ አባላዘር ተብሎ በሚጠራው በሽታ ውስጥ በሚካተቱ ኢንፌክሽኖች በ2022 በቀን አንድ ሚልዮን አዳዲስ ሰዎች እንደሚያዙ ነው የገለጹት፡፡ በዚሁ አመት በዚሁ በሽታ 230ሺህ ሰዎች ህወታቸውን አጥተዋል፡፡ኤችአይቪን በተመለከተ በ2020 ከነበረበት 1.5 ሚልዮን ወደ 1.3 ቅናሽ ያሳየ ቢሆንም በበሽታው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ግን ማሻቀቡ ነው የተሰማው። በ2022 630ሺህ ሰዎች ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን ሲያጡ ከእነዚህ መካከል 13 በመቶዎቹ እድሚያቸው ከ15 አመት በታች የሆኑ ህጻናት ነበሩ፡፡የኤችአይቪ ኤድስ ህክምና እና ክትትል ባለፉት አመታት በ73 በመቶ ጭማሪ ተመዝግቦበታል ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አዳዲስ የሚወጡ ሪፖርቶች የበሽታው አቅም ጨርሶ እንዳልተዳከመ የሚያመላክቱ ናቸው፡፡ይህን ተከትሎ የአለም ጤና ድርጅት ሀገራት በበሽታው ዙርያ ፖሊሲያቸውን እንዲከልሱ አሳስቧል።በተለይ በወጣቶች እና ታዳጊዎች አካባቢ ያለው ስርጭት አሳሳቢ በመሆኑ ወላጆች የልጆችን ሁኔታ እንዲከታተሉ ምክረ ሀሳቡን ሰንዝሯል፡፡በአሁኑ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ ወደ 39 ሚልየን የሚጠጉ ሰዎች ከቫይረሱ ጋር ሲኖሩ የምድርን የህዝብ ቁጥር 0.7 በመቶ የሚሽፍኑ ናቸው፡፡
Al-Ain
More Stories
የዞኑን ህዝብ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ሽፋን ወደ 45 % ለማድርስ አቅዶ 42% ማከናወን መቻሉን የሸካ ዞን ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ አሳወቀ።
የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ከኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዮሪ ሙሴቬኒ ጋር በመሆን ኢትዮጰያ እና ሶማሊያ የአፍሪካ ቀንድን ወደ አለመጋጋት ውስጥ ሊከት የሚችለውን ችግር በውይይት እንዲፈቱ ጥረት እንደሚያደርጉ በትናንትናው እለት መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የቴፒ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የከተሞች ፕላን ኢኒስቲትዩት ተገለጸ፡፡