November 23, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሃማስ መሪዎች የእስር ማዘዣ ወጣባቸው።

ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት በእስራኤል እና ሐማስ መሪዎች ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል

የእስር ማዘዣው የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እና የሐማስ ጦር አዛዦችንም ይመለከታል

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የእስር ማዘዣ ወጣባቸው፡፡

ሀማስ ከሳባት ወር በፊት በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ የተጀመረው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል።

ይህን ተከትሎ እስራኤል በሀማስ ስም በንጹሀን ዜጎች ላይ ጥቃት ከፍታለች የሚሉ አስተያየቶች ከተለያዩ ሀገራት እና ሰብዓዊ ተቋማት በመሰንዘር ላይ ናቸው።

እስራኤል ሀማስ ላደረሰው ጥቃት እየሰጠችው ባለው ራስን መከላከል ዘመቻ ከ35 ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን እንዲሁም ከ1 ሺህ 200 በላይ እስራኤላዊያን ተገድለዋል።

ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት በዚህ የንጹሃን ዜጎች ግድያ ተጠያቂ ናቸው ባላቸው መሪዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ አስተላልፏል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

እንደዘገባው ከሆነ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ዮቭ ጋላንት ከእስራኤል በኩል ከሐማስ በኩል ደግሞ ሶስት አመራሮች የእስር ማዘዣው ወጥቶባቸዋል፡፡

Al-Ain

You may have missed