November 23, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የክልሉን ህዝብ ጥያቄ መፍታት የሚያስችል አሰራር ለመፍጠር እየተሰራ ነው-አቶ ጥላሁን ከበደ

 ክልላዊ ራዕይ እውን ለማድረግ የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነት በመፍጠር የህዝባችንን ጥያቄ መፍታት የሚያስችል አሰራር ለመፍጠር እየሰራን ነው ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የከፍተኛ አመራሮች መድረክ “የክልላችን ህብረ ብሔራዊ አንድነት ለራዕያችን ስኬት” በሚል መሪ ሀሳብ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው።ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረክ እንደገለጹት ÷መድረኩ በክልሉ፣ በብልፅግና ፓርቲና በመንግስት የተከናወኑ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም መነሻ በማድረግ ወቅታዊ ሁኔታ በሚገባ ተረድቶ በቀጣይ የህዝቡን ጥያቄ መመለስ የሚያስችል ቁመና ላይ ለመድረስ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡መድረኩ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ÷የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ በጠንካራ የአመራር ቁመና ለመምራት በሚያስችል ስምምነት ላይ ይደረሳል ተብሏል።በመድረኩ ከርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተጨማሪ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

FBC

You may have missed