October 5, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማትና የዘርፉ አስፈፃሚዎች የ9 ወር ሥራ አፈፃፀም እየተገመገመ ነው

 የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት፣ የክልል የዘርፉ አስፈፃሚዎችና ባለድርሻ አካላት ያለፉት ዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡ባለፉት ዘጠኝ ወራት በአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አጠቃቀም፣ በአዳዲስ ኢንቨስትመንት ማስፋት፣ በኢንዱስትሪ ሽግግር፣ በጥናትና ምርምር ዘርፎች ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በመድረኩ ገልጸዋል፡፡የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን የዘርፉ ሞተር በማድረግ ዘርፉን ለማነቃቃት በታቀደው መሠረት የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡በዚህም የአምራች ኢንዱስትሪ ዋነኛው ሀገራዊ የርብርብ ማዕከል እንዲሆን ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት፡፡

FBC