November 21, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

“ኢትዮጵያ ትወዳደር፣ ተወዳድራም ታሸንፍ” በሚል መሪ ቃል

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲው በ21 ሚሊየን ብር ወጪ ያስገነባውን የአረጋውያን ማዕከል አስመረቀ።

ማዕከሉ 104 ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው አረጋውያንን የሚይዝ ሲሆን፤ ከዳያስፖራዎች፣ የግንባታ ተቋራጮች፣ ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና ከውስጥ ገቢ በተገኘ ገንዘብ የተገነባ ስለመሆኑ ተነግሯል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ (ዶ/ር) በምረቃ ስነ-ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ አገልግሎቱ የአረጋውያን መኖሪያ ቤት ማደስን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል።

ይህን ስራውን በማስፋት በቋሚነት አረጋውያንን ለመደገፍና ሰብዓዊ ክብራቸው ተጠብቆ ቀሪ ዘመናቸውን እንዲኖሩ ለማድረግ ማዕከሉ መገንባቱን አመልክተዋል።

በቀጣይም አረጋውያኑ የሕክምና አገልግሎት የሚያገኙበትን የሕክምና ማዕከል ለማስገንባት ዝግጅት መደረጉን ጠቁመው፤ ለስራው ዕውን መሆን ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ እታገኝ አሰፋ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ለአረጋውያን ማዕከል ማስገንባቱ ሀገራዊ ተልዕኮውን ለመወጣት የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያሳይ ገልጸዋል።

FBC

You may have missed