
ታራሚዎች የእርምት ጊዜያቸውን ጨርሰው ማህበረሰቡን ሲቀላቀሉ አምራች ዜጋ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን የድሬዳዋ ሁሉን አቀፍ ማረሚያ ቤት አስታወቀ፡፡ ማረሚያ ቤቱ ለሕግ ታራሚዎች የተለያዩ የሙያ ስልጠናዎችን በመስጠት በስድስት ማህበራት በማደራጀት የተለያዩ ምርቶችን ለገበያ እያቀረቡ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉን የማረሚያ ቤቱ ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር ወንድሙ ደበላ ገልፀዋል። የሕግ ታራሚዎቹ በብሎኬት፣ ፈሳሽ ሳሙና፣ የኤሌክትሪክ ምድጃ፣ የባህል አልባሳትና የፍራፍሬ ጭማቂ ለተጠቃሚዎች በማቅረብ ተጠቃሚ እየሆኑ መሆናቸውንም አመላክተዋል። በህግ ታራሚዎቹ ተመርተው ለገበያ የሚቀርቡት ምርቶች ከድሬዳዋ አልፈው ጅግጅጋ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጭሮ ከተማ ድረስ እየተሸጡ እንደሚገኙም ገልፀዋል። በማረሚያ ቤቱ ከሚገኙት ታራሚዎች ከፊሎቹ በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ ተሰማርተው ራሳቸውን በገቢ እንዲችሉና የእርምት ጊዜያቸውን ጨርሰው ማህበረሰቡን በሚቀላቀሉበት ወቅት አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
FBC
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ