ህብረተሰቡ በየደረጃው ከሚገኙ የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በአካባቢው ዘላቂ ሰላም በማስፈን የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ።
የሸካ ዞን ፀጥታ ምክር ቤት የ9 ወር እቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ የዞን ፣የወረዳ፣የከተማ አመራሮችና ሌሎች የፀጥታ አካላት በተገኙበት በማሻ ከተማ አካሂዷል ።
በመድረኩ የ9ወር የዕቅድ የአፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የሸካ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምርያ ሀላፊ አቶ ዘርሁን እምሩ እንደተናገሩት በዞኑ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ የፀጥታ አደረጃጀቶችን በማጠናከር በተሰራው ስራ የአካባቢውን ሰላምና መረጋጋት ማስጠበቅ ተችሏል ብለዋል ።
በዞኑ በአንድ አንድ አካባቢዎች ከቀበሌዎች ወሰን ጋር ተያይዞ ችግሮች እየተከሰቱ መሆኑን ገልፀው ይህንኑ ለመፍታት ህብረተሰቡን በማሳተፍ በኩል ባለድርሻ አካላት ልዩ ትኩረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል ።
ያለ ህብረተሰብ ተሳትፎ የአካባቢውን ሰላም ማረጋገጥ አይቻልም ያሉት አቶ ዘሪሁን አልፎ አልፎ እየታየ ያለውን ዝርፊያና የስርቆት ወንጀሎችን ለመከላከል ሁሉም ሰው አካባቢውን በንቃት ከመጠበቅ በተጨማሪ ከጸጥታ አጋላት ጎን በመሆን የመረጃ ለውውጥ በማካሄድ የዞኑን ሰላም ዘላቂ ማድረግ እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
በመድረኩ ባለድርሻ አካላትም የፀጥታ አካላት ተቀናጅቶ የለመስራት ችግር ፣ የመረጃ ልውውጥ ላይ ክፍተቶች መኖር ፣ በከተሞች የተለያዩ ዝርፍያዎች መበራከት ፣ ጠጥቶ በመስከር ወንጀል መበራከት ፣ የዝርፊያ ወንጀሎች መበራከት በአጎራባች ወረዳዎች በልማት አማካይነት የወንጀል መበራከት እንዲሁም እየተከሰቱ ያሉትን ወንጀሎችን በአፍጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሎጅስቲክና ሌሎች መሠል ችግሮችን በስፍት በማንሳት ለነዝህ ችግሮች መፍተሔ ለማበጀት በቀጣይ እንደምሰራ ተናግሯል ።
የቁማርና የሽሻ ቤቶች በከተሞች መበራከት ፣ለምልሻዎች የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች አለመስጠት፣በትራንስፖርት ዘርፍ እየታዩ ያሉ ችግሮችም ሊፈቱ እንደሚገባ ጠይቀዋል ።
በመድረኩን የመሩት የሸካ ዞን አሰተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ በበኩላቸው አሁን ላይ በዞኑ እየታየ ያለውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ በየ ደረጃው የሚገኙ የፀጥታ አካላት ህብረተሰቡን በማሳተፍ በአካባቢው ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ ወንጀሎችን በጋራ መከላከል እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
የአካባቢውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ የፀጥታ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ለፀጥታ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን ቀድሞ ለይቶ በመከላከል ረገድ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል ።
ለቀጣይ በዘርፉ እየታዩ ያሉ ችግሮችን በመለየት በዬ ደረጃው የምገኙ የፀጥ አካላትን አደረጃጀት በማጠናከር ከህብረተሰቡ ጋር የመረጃ ልውውጦችን በማካሄድ የዞኑን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ የተጀመሩ መልካም ስራዎችን ማጠናከር እንደምገባ በአፅንኦት ገልፀዋል ።
በመድረኩ እንደ ችግር የተነሱትን በየ ደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ምላሽ የሰጡበት ሲሆን በተለይም የወረዳ አስተዳዳሪዎችም ህገ-ወጥ የመሬት ወረራና የቀበሌዎች የወሰን ጋር ተያይዞ አልፎ አልፎ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን ለቀጣይ ልዩ ተኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
በመድረኩም የሸካ ዞንና የወረዳ አስተዳደሪዎች እንዲሁም የፀጥታ ፅ/ቤት ሃላፍዎችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ።
ዘጋቢ አስቻለው አየለ
More Stories
የቴፒ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የከተሞች ፕላን ኢኒስቲትዩት ተገለጸ፡፡
የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተመረጡ የግብርና፣ በቱሪዝም፣ በቴክኖሎጂ እና ማዕድን ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበየቻይናዋ ግዛት ከፍተኛ ልዑካን የተሳተፉበት የቻይና-አፍሪካ (ኢትዮጵያ) የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝም ና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በዓለም ለ45ኛ በኢትዮጵያ ለ37ኛ በክልሉ ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረዉ የዓለም የቱሪዝም ቀን ”ቱሪዝም ለሰላም” በሚል መር ቃል በቦንጋ ከተማ እየተከበረ ነዉ።