ማሻ ፣ የሚያዝያ 19፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ለ45ኛ ጊዜ ዛሬ በተደረገው የለንደን ማራቶን አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበላይነት አጠናቃለች።
በአለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው ማራቶን 2 ሰአት 15.50 አትሌት ትዕግስት አሰፋ ርቀቱን ለማጠናቀቅ የወሰደባት ሰአት ነው።
ባለፈው አመት የለንደን ማራቶን 2ኛ የወጣችው ትዕግስት አሰፋ በዚህ አመት አሸናፊ ሆናለች።
በጉዳት ብዙ የተፈተነችው የቀድሞዋ የ800 እና የ1500 ሜትር አትሌት ከውድድሩ በፊት እንደተናገረችውም በለንደን ጎዳናዎች ከኬንያዊቷ ጆይሲሊን ጅፕኮስጊ እስከ መጨረሻው የገጠማትን ፉክክር ተቋቁማ አሸናፊ ሆናለች።
አትሌት ትዕግስት አሰፋ በሴቶች ብቻ (women only) የአለም ክብረ ወሰንን በመስበር ነው ያሸነፈችው
የሁለት ጊዜ የበርሊን ማራቶን አሸናፊዋ አትሌት በርቀቱ ከኬንያዊቷ ሩት ችፕንጌቲች በመቀጠል የአለም 2ኛው ፈጣን ስአት ባለቤት እንደሆነችም ይታወቃል።
ኬንያዊቷ ጆይሲሊን ጅፕኮስጊ 2ኛ ወጥታለች።
የ2021 የለንደን ማራቶን አሸናፊዋ ጅፕኮስጊ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 2 ሰአት 18 ደቂቃ 41 ሰከንድ ወስዶባታል
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን ሀሰን ደግሞ 3ኛ ወጥታለች::
ኢቢሲ
More Stories
በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሙስናን ለመከላከል በተደረገው ጥረት ከ85 ሚሊዮን በላይ ብር የህዝብ ሃብት ማዳን ተችላል
ኢትዮጵያ እና ኢንግሊዝ በኢንቨስትመንት፣ በንግድ እና ኢኮኖሚ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ ተስማሙ
272 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ