April 3, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ግብርንና ታክስን በታማኝነነት የሚከፍል ዜጋን የመፍጠር ግብ የሚሳካው በተቀናጀ ርብርብ ነው

ማሻ ፣ የመጋቢት 20፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ህይወት አሰግድ የደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክልል ገቢዎች ቢሮ ከኢፌዴሪ.የገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት የተዘጋጀው ክልላዊ የታክስና ጉምሩክ ክበብ ተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር መድረክ በደማቅ ሁኔታ ተካህዷል።

የታክስ ሞራሉ የተገነባ ትውልድ ለጤናማ ፍትሃዊ የታክስ ስርዓትና ለሀገር ልማት፣ ከመሰረቱ የተገነባ ትውልድ ሀገርን ይገነባል በሚሉ መርህ ቃላት ነው መድረኩ የተካሄደው።

ራስን የመቻል ሀገራዊ ራዕይን ለማሳካት የተቀናጀ ርብርብ መጠናከር እንዳለበት የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሀላፊዋ ወይዘሮ ህይወት አሰግድ አስገንዝበዋል።

በዘንድሮ አመት እንደ ክልል 10.071 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን የጠቆሙት ሃላፍዋ ይህንን ግብ ለማሳካት ትኩረት ከተሰጠባቸው ተግባራት መካከል የግብር ከፋዩን ግንዛቤ ማሳደግ ዋናው መሆኑን ጠቅሰዋል ።

የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር በሁሉም ትምህርት ቤቶች መካሄዱን ገልፀው አሸናፊ ተወዳዳሪ ክልሉን ወክሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሳተፍ ጠቁመዋል።

በክልል አቀፍ ውድድሩ የተሳተፉ ተማሪዎች በንቃት ተሳትፈውበታል ።

በፈዴራል ገቢዎች ሚኒስቴር የጅማ ቅርንጫፍ ምክትል ስራአስኪያጅ አቶ ነጋሶ አብድሣ በበኩላቸው የክልሉ ገቢዎች ቢሮ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑን ገልፀው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስገንዝበዋል።