ማሻ ፣ የመጋቢት 18፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ውይይቱን የመሩት የማሻ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ሓላፊ አቶ አስማማው ነችቶ እንደገለፁት በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ወጣቱ የራሱን ሚና መጫወት እንዳለበት ገልፀው በሁለተኛ መደበኛ ጉባኤው በጠንካራ ጉን የተነሱትን በማስቀጠል ና በድክመት የተነሱ ጉዳዮች ላይ ወጣቱ ጋር በመነጋገር ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት ነው ብለዋል።
ወጣቱ የከፋፋይ ትርክት በመተው የወል ትርክትን ለመገንባት የሚዲያ አጠቃቀምና ኮሚኒኬሽን ስራን ለሀገር ግንባታ መጠቀም ይጠበቅበታል ብለዋል።
አቶ አስማማው አክለውም ወጣቱ የአካባቢውን ፀጋ በመጠቀም ወደ ኢኮኖሚ መለወጥ እንዳለበትም አሳስበዋል ።
የውይይቱ ሰነድ ያቀረቡት የብልጽግና ፖርቲ ወጣቶች ክንፊ ሓላፊ ትዕግስት አበራ በመደመር ዕሳቤ በማድረግ ሁለተኛውን መደበኛ ጉባኤ ውሳኔና አቅጣጫ ዎች መሠረት የሰላም ግንባታ ስራ ማጠናከር፣በፍትህ ዘርፍ ውጤታማ ስራ ማጠናከርና ጠንካራ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ስራ መስራት በሰነዱ ከተመላከቱት ሀሳቦች መካከል ናቸው።
በውይይቱ የተሳተፉ ወጣቶች መካከል መሠረት በቀለናመክብብ መኮንን እንደገለፁት የወጣቶችን አደረጃጀት ማጠናከር ፣ የወጣቱ የስራ ባህል ለማሳደግ ና የስራ ዕድል ለመፍጠር በቅርበት ድጋፍ መስጠት፣ ሀገር በቀል ዕሳቤዎች ማሳደግና አካታችነት ላይ በትኩረት መሠራት አለበት ብለዋል ።
በማጠቃለያው የማሻ ከተማ ከንቲባ አቶ ሠራዊት አየነው የውይይቱ ዓላማ ብልፅግና የምመራው መንግስት ሀገራዊ ወጥ የሆነ ግንዛብ ለመያዝ መሆኑን ገልፀው የከተማ ልማትን ለማስቀጠል ወጣቱን በማማከርና የጋራ ግንዛቤ በመያዝ እንደምሰራ ጠቁመዋል ።
More Stories
የዘመናት የማሻ ከተማና አካባቢው ህዝብ ጥያቄ የነበረው የመብራት አቅርቦት ችግር የሚፈታ የሳብስቴሽን ግንባታ አልቆ መብራት የማብራት ሙከራ ስራ በስኬት ተጠናቀቀ
የለውጥ ዓመታቱ በፖለቲካ ምህዳራችን አካታችነትና አቃፊነት የተረጋገጠበት ነው- አደም ፋራህ
የሸካ ንጉስ ቴቺ ቄጃቺና የምክራቾ አባላት በማሻ ወረዳ ከሚገኙ የጎሳ መሪዎች ጋር ዉይይት አካሄዷል።