ማሻ ፣ የመጋቢት 16፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም )በስድስት ክላስተር እና ወረዳ ፖሊስ መካከል ለ5ቀናት የተደረገው ወረዳ አቀፍ የእግርኳስ ጨዋታ ተጠናቋል።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የማሻ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና መንገድ ትራንስፖርት ደህንነት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተግባሩ እዳሮ ጨዋታው ፍጹም ስፖርታዊ ጨዋነት በተላበሰ መልኩ እንዲጠናቀቅ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበው በዞን ደረጃ ለምካሄደው ውድድር ወረዳውን የሚወክሉ ስፖርተኞች የሚመለመሉበት ነው ቡለዋል።
የማሻ ወረዳ ባህል ቱሪዝም ስፖርት ጽ/ቤት ሀላፍ አቶ ባህሩ ተስፋዬ የውድድሩ ዓላማ የማሻ ወረዳን ለዞን ሻፒዮና የሚወክኬ ስፖርተኞች መመልመል እንደሆነ ተናግረዋል።
አበሎ ክላስተርን ከወረዳው ፖሊስ ያገናኘው የፍጻሜ ጨዋታ በአበሎ ክላስተር 4ለባዶ በማሸነፍ ዋንጫውን ያነሳ ስሆን የይና ክላስተር የፀባይ ዋንጨ ተሸላም በመሆን ጨርሰዋል።
በዚህም መሠረት ልዑል እሸቱ ኮከብ ተጫች ሆኖ ስመረጥ ልዑል መኮንን እና አንድነት ሻወኖ በጋራ ኮከብ ጎል አግብ በሆነው ውድድሩ ተጠናቆዋል።
More Stories
የዋልያዎቹ ድል ለቀጣይ ጨዋታ አቅም ይሆነናል – አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ
ኢትዮጵያ በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከዓለም 3ኛ በመሆን አጠናቀቀች
በሴቶች 1500 ሜትር ኢትዮጵያ የወርቅ እና ብር ሜዳሊያ አገኘች