April 3, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የክልሉ ሱፕርቭዥን ቡድን በማሻ ወረዳ በመንግስትና ፓርቲ እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት የመስክ መልከታ አካሂዷል ።

ማሻ ፣ የመጋቢት 15፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ የተመራ ልዑክ በይና፣ ጋዳና ጋቲሞ ቀበሌዎች በበጋ ስንዴ ልማት፣በኩታ ገጠም የአትክልት ማሳና የማር መንደር ልማት የመስክ ምልከታ አካሂዷል ።

የክልሉ ሱፕርቭዥን ልዑክ የመሩት አቶ ፋንታሁን ብላቴ በዞኑ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች ያለበትን ደረጃ በሪፖርት ከማዳመጥ ባለፈ ተግባራት ያሉበትን ሁኔታ አስከታችችኛው መዋቅር ድረስ ለመመልከት እንደሆነ ተናግረዋል ።፧

በመንግስትና ፓርት ስራዎች የይና ቀበሌ የሚበረታታ መሆኑን ገልፀው በግብርና ስራዎች ወረዳው ያለው አቅም ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል ።

በወረዳው በበጋ ስንዴ፣ በአትክልት ስራ፣ በንብ ማነብና እንሰት ልማት የተሰሩ ተግባራት የሚደነቅ መሆኑንም ገልፀዋል።

ሀላፊው አክለው በይና ቀበሌ በፓርቲው መሪነት በልማት ህብረት በመደራጀት የተሰራው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀው በቀጣይ መንግስት ባስቀመጠው የትኩረት አቅጣጫ መሠረት አርሶ አደሩን በቅርበት በመደገፍ ምርትና ምርታማነት ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል።

በክልሉ በማህበራዊ ዘርፍ የርዕሰ መስተዳድሩ አማካሪ አቶ ደነቀ ማሞ በጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ ኢንሸቲቭ የተጀመረው የስንዴ ልማት በይና ያለው አፈፃፀም የሚበረታታ መሆኑን ገልፀው ከጤና አንፃር የአርሶ አደሩ የንፅና አጠባበቅ ስራ ጥሩ መሆኑን አንስተዋል ።

በቀጣይም የጤና መድህን ተግባራት በትኩረት መስራትና በወተት ልማት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ምርታማነት ማሳደግ እንደምገባ ተናግረዋል ።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊና እንስሳትና አሳ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ታመነ በቀለ በበኩላቸው በእንሰት ልማት የተሰሩ ስራዎች ተጠናክሮ እንድቀጥል ጠይቀው ያሉትን መሬቶች አሟጦ ከመጠቀም አንፃር በትኩረት መሠራት አለበት ብለዋል።

በቀጣይም በልማት ትሩፋት ተግባራት አርሶ አደሩ አስፍቶ በመስራት ቴክኖሎጅን በመጠቀም ምርታማነትን ለማሳደግ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

በመስክ መልከታው ወቅት ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች መካከል አርሶአደር ታደለ አዳዎ እና ሼናችራሻ ገቦ ዳሾ እንደገለፁት የክልሉ ሱፕርቭዥን ቡድን እስከታች ወርዶ የልማት ስራዎችን መመልከቱ እንዳስደሰታችው ገልፀው በቀጣይ መንግሥት የንብ እርባታ ግብዓትና ለሎች የግብርና ተክኖሎጂ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል ።

በመስክ ምልከታው የክልሉ ባህል፣ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ ፣ በክልሉ በማህበራዊ ዘርፍ የርዕሰ መስተዳድሩ አማካሪ፣ የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊና የእንስሳትና አሳ ዘርፍ ኃላፊ ጨምሮ ለሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ።