March 14, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሮናልዶ ከፕሬዚዳንትነት ምርጫ እራሱን አገለለ

ማሻ፣ መጋቢት 4፣ 2017 (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) የቀድሞው የብራዚል እና ሪያል ማድሪድ አንጋፋ ተጫዋች ሮናልዶ ሉዊስ ናዛሪዮ ዲሊማ ከሀገሩ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነት ምርጫ እራሱን ማግለሉን ይፋ አደረገ፡፡

የ48 ዓመቱ የቀድሞ ዝነኛ ተጫዋች፤ የወቅቱን የብራዚል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኤድናልዶ ሮድሪጌዝ ለመተካት በሚደረገው ምርጫ በዕጩነት እንደሚቀርብ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ከሀገሪቱ ክልሎች የሚጠበቀውን ያህል ድጋፍ አለማግኘቱን ገልጾ፤ ከውድድሩ እራሱን ማግለሉን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አሳውቋል፡፡

“በብራዚል ካሉ 27 የክልል ፌዴሬሽኖች 23 ያህሉ ሊያናግሩኝ እንኳን አልፈቀዱም፤ አብዛኛው ውሳኔ ሰጪ አካል የሀገሬ እግር ኳስ በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን ካመነ እራሴን ከውድድሩ አግልያለሁ” ብሏል፡፡

የባሎንዶር እና የሁለት ጊዜ ዓለም ዋንጫ አሸናፊው ሮናልዶ፤ የሀገሩን እግር ኳስ ከፍ ለማድረግ የብራዚል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ለመሆን ቢፈልግም ሁኔታዎች ሳይፈቅዱለት ቀርተዋል፡፡

ኤፍ ኤም ሲ

ይህን ተከትሎም የወቅቱ የብራዚል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኤድናልዶ ሮድሪጌዝ በቀጣዩ ዓመት በሚደረገው ምርጫ ብቸኛ ዕጩ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡