ማሻ ፣ የመጋቢት 04፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸው የፕሪቶሪያ ስምምነት ተግባራዊ እንዳይሆን ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮችን ለመፍታት መሰራት እንዳለበት አመላክተዋል፡፡
ለክልሉ አላስፈላጊ ገፅታ የሰጡትን ያለፉ ድርጊቶች ማረም ሲገባ በተቃራኒው ሁኔታውን እያባባሱ ያሉ አካላት ከአፍራሽ እንቅስቃሴያቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ይህ ሕገወጥ እንቅስቃሴ ክልሉን ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱን የሚጎዳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚህ ሕገወጥ እንቅስቃሴ ምክንያት የክልሉ ነዋሪ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እያለፈ መሆኑን ያነሱት አቶ ጌታቸው፤ ይህም የግጭት አስከፊ ገፅታ ማሳያ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የትግራይ ህዝብ ዘላቂ ሰላም ይገባዋል ያሉት አቶ ጌታቸው፤ ከህዝብ ጥያቄ በላይ የስልጣን ጥያቄን የሚያስቀድሙ ግለሰቦች ክልሉን ለባሰ አዘቅት እየዳረጉት ነው ብለዋል።
የፕሪቶሪያ ስምምነት ተፈፃሚነት ከሚገባው በላይ ጊዜ መውሰዱን አንስተው፤ ይህም የክልሉ መረጋጋት የግል ጥቅማችንን ያሳጣናል በሚሉ አካላት ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።
የፌደራል መንግስት እና የሚመለከታቸው አካላት የጦርነት አማራጭን ለማስቀረት የሚያስችሉ ሁሉንም አስፈላጊ እርምጃዎች እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ኢቢሲ
More Stories
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
የፆታ እኩልነትን በማረጋገጥ የሚታዩ ክፍተቶችን በማረም ውጤታማ ለውጥ ማስመዝገብ እንደሚገባ ተገለፀ ።
ተከታታይ ሦስት ቀናት ስካሄድ የነበረው የግብርና ባለሙያዎች ግምገማ ነክ ውይይት አጠቃላይ 119 ባለሙያዎች በህስ ፤ በማስጠንቀቂያ እና በድስፕሊን እንዲጠየቁ በማድረግ ተጠናቀቀ።