March 14, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ተከታታይ ሦስት ቀናት ስካሄድ የነበረው የግብርና ባለሙያዎች ግምገማ ነክ ውይይት አጠቃላይ 119 ባለሙያዎች በህስ ፤ በማስጠንቀቂያ እና በድስፕሊን እንዲጠየቁ በማድረግ ተጠናቀቀ።

ማሻ ፣ የመጋቢት 03 ፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም ) የማጠቃለያ መድረኩን የመሩት የሸካ ዞን ግብርና መምረያ ሀላፍ አቶ አዕምሮ ደሳልኝ እና የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፍን አዳሾ እንደገለፁት የግብርና ባለሙያዎች አገልግሎት መቀዛቀዝ በግብርና ተግባር ላይ ያሳደረውን አሉታዊ ተፅዕኖን ለመቅረፍ ያስፈልጋል ብለዋል።

በዚህም የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችንን በማሻሻል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በሀገር ደረጃ የታየውን የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል ።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፍን አዳሾ እንደገለፁት በየዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች የሙያውን መብትና ግደታ በመረዳት ከዚህ በኋላ ባለው ጊዜ በግምገማው የተቀመጡ አቅጣጫዎችንና ትምህርቶችን ተግባራዊ በማድረግ የተሻለ አፈጻጸም ማሳየት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

የግምገማው ውጤት በተመለከተም አጠቃላይ የተገመገሙ ወንድ 67 ሴት 52 በድምሩ 119,የተገመገሙ ሲሆን በማስጠንቀቂያ ወንድ 15 ሴት 10 በድምሩ 25 እና በዲስፕሊን ወንድ 1 እንዲሁም ፤ በህስ ወንድ 51 ሴት 42 በድምሩ 93 ባለሙያዎች እንዲጠየቁ ውሳኔ የተወሰነ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል።

በመድረኩም የግብርና ባለሙያዎች ችግር ፈች ድጋፍ ያለማድረግ፣ የኤፍቲስ ማሳዎችን ሞዴል ያለማድረግ ፤ ዉሎአድሮ በቦታው ተተክሎ አለመስራት ፤ የግባዓት አቅረቦ ችግር ፤ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዝቅተኛ መሆን ፤ የሕግ-ወጥ መሬት ወረራን ያለመከላከል ፣ በክህሎትና በባለሙያ የሥራ ሥነ-ምግባር ችግር እንዲሁም በማስፈጸም ረገድ የሚታዩ ውስንነቶች በግምገማ ላይ በሰፊው ተነስቷል።

በመድረኩም የክልል ፣ የዞንና የወረዳ አጠቃላይ አመራሮች ጨምሮ የ19ኙ ቀበሌ አስተዳዳሪዎችና የፓይለት አመራሮች እንዲሁም የግብርና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

ወረዳ ኮሚኒኬሽን