March 14, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ማሻ ፣ የመጋቢት 03 ፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም ) የበጎ አድራጎት ስራ ከሚሰሩ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድጋፍ ከሚያደርግላቸው ተቋማት አንዱ የሆነው ባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት በተያዘው የረመዷን ወር ለተቸገሩ ወገኖች ያውለው ዘንድ የ15 ሚሊዮን ብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማዕከሉ በመገኘት ድጋፍ አድርጓል።

ባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት በቀን ከ4 ሺህ 800 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የምገባ አገልግሎት እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መረጃ ያመለክታል።

ኢቢሲ