ማሻ ፣ የመጋቢት 03 ፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም ) ኢትዮጵያ ለንግድና ኢንቨስትመንት መጎልበት በትኩረት እየሰራች ነው ሲሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም ኤምባሲ የልማት ዳይሬክተር ፖል ዋልተርስ የተመራን ቡድንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ኢትዮጵያ ለንግድና ኢንቨስትመንት መጎልበት በትኩረት እየሰራች መሆኗንና ከመቼውም ጊዜ በላይ አስቻይ ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበናል ሲሉ ለልኡካን ቡድኑ መግለጻቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደም ጠንካራ የንግድ ግንኑነት ያላቸው ሀገራት ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ ሚስተር ፓል በበኩላቸው ዩናይትድ ኪንግደም ኢትዮጵያ እያሳየች ላለችው የኢኮኖሚ ሪፎርም ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል ሲሉም ገልጸዋል።
ለአለም ንግድ ድርጅት አባልነት እያደረግን ያለውን ዝግጅትም አድንቀዋል ብለዋል፡፡
በሁለትዮሽ የገበያ ዕድሎች ዙሪያ በቀጣይነት በጋራ በምንሰራባቸው አግባቦች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል ሲሉም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
ኢዜአ
More Stories
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
ትራምፕ በብረት እና አልሙኒየም ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ታሪፍ ጣሉ
ከውጭ ባንኮች ጋር ለመወዳደር እየተዘጋጁ መሆኑን ባንኮች ገለጹ