February 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊቨርፑል ከአስቶን ቪላ ጋር ይጫወታሉ

ማሻ፣ የካቲት 12፣ 2017 (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት አስቶን ቪላ ከሊቨርፑል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

ምሽት 4፡30 በሚካሄደው ጨዋታ አስቶን ቪላ በሜዳው ሊጉን በመምራት ላይ የሚገኘውን ሊቨርፑል የሚገጥም ይሆናል፡፡

በጥሩ የዝውውር መስኮት ንቁ ተሳታፊ የነበሩት እና ጠንካራ ተጫዋቾችን ያስፈረሙት ቪላዎቹ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት እየተፋለመ ለሚገኘው ሊቨርፑል ፈተና እንደሚሆኑበት ይጠበቃል።

በጨዋታው ከሊቨርፑል በኩል ኮዲ ጋክፖ እና ጆ ጎሜዝ በጉዳት ምክንያት እንደማይሰለፉ ተመላክቷል፡፡