የአርብቶና ከፊል አርብቶ አደር ልጆችን በሆስቴሎች 179 ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ መሆናቸው
በአርብቶ አደር አካባቢ የሚታየውን የተማረ የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ በመጀመሪያ ዲግሪ 116 እና በዲፕሎማ 42 ተማሪዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑ
በአነስተኛ የመጠጥ ውሃ ስራዎች የምንጭ ግንባታ ቤሮ ወረዳ ሲሪት ቀበሌ፣ ሜ/ሻሻ ወረዳ ቂራ ቀበሌ፣ ሜ/ሻሻ ወረዳ ጎሪነሱ ቀበሌ፣ ሜ/ሻሻ ወረዳ ቦኡት ቀበሌ 100% የተጠናቀቁ መሆናቸው
የመንገድ መሠረተ ልማት ሽፋን ለማሳደግ 18 ኪ/ሜ ከባቹማ እስከ ጨበራ DC-2 የጠጠር መንገድ ግንባታ በማጠናቀቅ አገልገሎት እንዲሰጥ ተደርጓል
44 ኪሎ ሜትር ከሀዱባ-ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሶስት መንገድ ከፈታ ሥራ 50% ማድረስ መቻሉ፡፡
20 ኪሎሜትር ቱልጊ- ካሪ -ሞጋ DC-2፣ 31 ኪሎሜትር ከኡፊት ጋራሙጂ DC-2 እና 30 ኪሎሜትር ከጨበራ ያርጣ DC-2 የጠጠር መንገድ ግንባታ የጨረታ ዶክመንት ዝግጅት ተፈጽሟል
የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ሥራ 45 ኪሎሜትር ከአደይ አበባ ፎልጁ፣ 60 ኪሎሜትር ከኩምባ -ኦሽካ ዲንቻ-ኮንታ፣ 52 ኪሎሜትር ሞጋ -ናምሪ፣ 50 ኪሎሜትር ጎሪ ጌሻ-ጨለማ ሸጥ መንገድ ጥናትና ዲዛይን ሥራ ተጀምሯል
ድልድይ ጥናትና ዲዛይን ስራ 5 ድልድይ (ማሙሩ፣ ዴካ፣ ሾሻሮ፣ ሹሪ እና ኩጃጉዱ) 85% መድረሱ
በአርብቶ አደሩ አካባቢ የመስኖ ልማት ከ 150 ሄ/ር የሚያለማ የኪሉ አነስተኛ መስኖ ግንባታ 78% መድረሱ
በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ስራዎች በመሬት ልማትና ማኔጅመንት በክልሉ በሚገኙ ከተሞች 377.64 ሄ/ር የለማ መሬት መዘጋጀት መቻሉ
2,039 ሰነድ አልባ ይዞታዎች ሰነድ እንዲያገኙ ተደርጓል
በከተሞች መሠረተ-ልማት ግንባታ ነዋሪዎች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ ህብ/ሰቡ 59,889,110 ብር የሚገመት የገንዘብ፣የጉልበትና የቁሳቁስ አስተዋጽኦ ማበርከት መቻላቸው
የክልሉን ህዝብ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ስራዎች በከተማና በገጠር ክልላዊ የዉሃ ሽፋን ከነበረበት ወደ 43.73% ማድረስ መቻሉ፡
በማዕድን ሃብት ልማት ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚውሉ 50,406 ቶን የድንጋይ ከሰል ማምረት መቻሉ፡፡
የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ለማሳደግ በባህላዊ እና በልዩ አነስተኛ ወርቅ አምራቾች ምርትና ግብይት ዙሪያ በተካሄደው እንቅስቃሴ 75.525 ኪ.ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ መቻሉ፡፡
የመስኖ አውታሮች ግንባታ ሽፋንን ከ3641 ሄ/ር ወደ 3856.5 ሄ/ር ለማሳደግ በዘላቂ ልማት ግቦች ማሳኪያ ፕሮግራም 5 ነባር መስኖ ፕሮጀክቶች እና 1 አዲስ ጥገና ( ዳማ፤ ኦልሙ፤ ፅልቤ፤ ውኒ ፤ ሻታ እና ሸዉ ጥገና ) እየተሰሩ መሆኑ
በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም 1077 ሄ/ር መሬት ማልማት የሚያስችሉና 1333 አ/አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የ10 አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ሥራን በማከናወን በአማካይ ከነበረበት 34.9% ወደ 43.3% ማድረስ መቻሉ
የትራንስፖርት መሰረተ-ልማት ፍትሃዊ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በክልሉ በጀት እየተገነቡ ያሉ 3 መናኸሪያዎች ፊዚካል አፈጻጸም የቦንጋ መናኸሪያ 60% ፣ የሚዛን መናኸያ 72% እንዲሁም የታርጫ መናኃሪያ 83% ማድረስ ተችሏል፡፡
በሁሉ አቀፍ ገጠር ተደራሽ መንገድ ግንባታ የድልድይ እና መንገድ ግንባታ አቅርቦትን ለማሳደግ የሚገነቡ የድልድይ እና መንገድ ፕሮጀክቶችን የመምረጥና ቀሪ ሥራዎችን የመለየት ሥራ መከናወኑ
በግማሽ ዓመቱ ለግንባታና ጥገና ስራ ከህብረተሰብ ተሳትፎ 116,995,380 ብር መሰብሰብ መቻሉ፡፡
በመንገዶች ባለስልጣን የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም- በሚዛን ዲስትሪክት 38.6 ኪ.ሜ ፣ በታርጫ ዲስትሪክት 12 ኪ.ሜ ፣ በቦንጋ ዲስትሪክት 24 ኪ.ሜ መገንባቱን ርዕሰ መስተዳድሩ አቅርበዋል።
ክ/መ/ኮ/ጉ ቢሮ
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።