February 1, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የመስኖ ልማት ስራዎችን በትኩረት እየሰራ መሆኑን በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ ግብርና አከባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ጽ/ቤት አስታወቀ ።

ጽ/ቤቱ በመደበኛ የመስኖ ተግባራት 1ሺህ 2መቶ ሄክታር መሬት ማልማቱንም ገልጸዋል።

በየዓመቱ ከዘርፉ የሚገኘዉ ዉጤት እየተሻሻለ መምጣቱን የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አክሊሉ ሸነኖ ገልጸው በተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኙ የዉሃ አማራጮችን በመጠቀም ዘርፈ ብዙ ተግባራቶች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

ዘመናዊ የአሰራር ዘዴዎችን በመከተል በመደበኛ መስኖ ስራ ድንችና ጥቅል ጎመንን ጨምሮ ሌሎች አታክልቶችን 1ሺህ 2መቶ ሄክታር መሬት ላይ ማልማት መቻላቸውንም ኃላፊ ተናግረዋል።

ከዚህም ባሻገር 1መቶ 65 ሄክታር መሬት ላይ የበጋ መስኖ ስንዴ አየለማ መሆኑንና በቀጣይም ሽፋኑን ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ አቶ አክሊሉ ገልጸዋል።

ካነጋገርናቸዉ አርሶ አደሮች መካከል የጨጋቻ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ አስረስ አምበሎና የሸክበዶ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ጌታሁን ጪዶ በበኩላቸው ከበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የሚገኘዉ ዉጤት እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዉ በቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ ተናግረዋል ።