February 1, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራን ለማጠናከር  የተጀመረው ስራ ላይ ሁሉም የነቃ ተስትፎ እንዲያደርግ የማሻ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ መስፍን አዳሾ ጥሪ አቀረቡ።

ይህ የተባለው የማሻ ወረዳ  ግብርና ደን  አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ጽ/ቤት  የ2017  የተፋሰስና የበልግ ልማት የንቅናቄ መድረክ በተካሄደበት ወቅት ነው።

የማሻ ወረዳ ግብርናና ደን አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ልሳኑ አለማየሁ እንደገለጹት የባለፈው ዓመት መልካም ተግባራትን በማጠናከር በጉለቶች ዙሪያ የጋራ ርብርብ በማድረግ ወደ ተግባር መግባት ይጠበቅብናል ብለዋል።

እንደ ክልል”የአፈር ሀብታችን ለብልጽግናችን ”  በሚል መሪ ቃል የ2017 የተፋሰስ ልማት ስራ በይፋ መጀመሩን ተከትሎ  በወረዳው ደገሌ ቀበሌ  ላይ መበሰሩን አስታውሰዋል።

የዘንድሮ የተፋሰስ ልማት ስራ ላይ ከሁሉም ማህበራዊ መሰረቶች  የተወጣጡ ከ17 ሺህ በላይ የህበረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉም  ኃላፊው ተናግረዋል።

በንቅናቄ መድረክ ላይ የ2016 ዓ.ም የተፋሰስ ልማትና  የበልግ አፈጻጸም ሪፖርቶች በዘርፉ ባላሙያዎች  ቀርቦ ሰፊ  ውይይትም ተደርጎበታል።

በወቅቱ ከተስተዋሉ ችግሮች መካከል የስራ ቀናትን በአግባቡ ያለመጠቀም፣ የሚከናወኑ ተግባራት   ላይ የጥራት ችግር መስተዋል፣ የመረጃ ልውውጥ የተጠናከረ አለመሆን፣ ሳይንሱን ያልጠበቁ ተግባራት መፈጸምና ሌሎችም ተነስተዋል።

በዚህ መነሻ ዘንድሮ 30 የስራ ቀናቶችን በአግባቡ በመጠቀም  5 ሺህ 3መቶ 79 ሄክታር በላይ የአፈርና የውሃ ጥበቃ ስራዎችን ለማከናወን ግብ መያዙም ተነስተዋል።

እንደ ወረደ በተፋሰስ ልማት ለማከናወን ከተያዙት ዕቅዶች መካከል  ደንን መልሶ ማካለል፣  የቡና ነቀላና ጉንደላ ፣ የአፈር ናሙና መሰባሰብ ፣የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ልማት፣ ድልድይ ስራና ሌሎችም በተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ይከናወናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከበልግ ልማት አንጻር በ 2016 ዓ.ም 6410 የነበረዉን   ወደ በ10ሺህ ሄክታር ማድረስ የተፈለገው በሁሉም አማራጮች  አርሶ አደሩን ምርታማ ለማድረግ እንደሆነም ተገልጸዋል።

በተለይ ወረዳው ለእንሰት ምርት ተስማም በመሆኑ ካለፈው አመት ጀምሮ  በተፈጠረዉ ንቅናቄ የተሻለ አፈጻጸም በመመዝገቡ ዘንድሮ 4 ሺህ ሄክታር ለመትከል መሬት መዘጋጀቱንና ለስራው ስከታማነት ለእያንዳዱ አርሶ አደር በነፍስ ወከብ ዕቅድ ተሰጥቶ ለስከታማነቱ ክትትል እየተደረገ ይገኛል።

የምርጥ ዘር አቅርቦት ችግር፣ የኩታ ገጠም  እርሻ ዘዴን ተግባራዊ አለማድረግ፣  ለደረሱ የእንሰት ችግኞች የገበያ ትስስር ያለመፈጠር፣  ሰብሎችን የሚያድሙ በሽታዎችን ከመከላከል አንጻር ውስንነቶች መኖርና ሌሎች ችግሮችም ከበልግ አንጻር ተነስተዋል።

የማሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፍን አዳሾ በበኩላቸው በሀገራችን የተፋሰስ ልማት ስራዎች ከተጀመረ  15 አመታት መቆጠሩንና በዚህም   እንደ ወረዳ በርካታ ውጤቶች መዝገቡን ገልጸዋል።

በወረዳው እየተመዘገቡ ላሉ ውጤቶች  ለዘርፉ ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበው  በተለይ ለእንሰት የተሰጠው ትኩረቱ ከዳር እንዳደርስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት እንዲያደርግ ጥሪ አቅቧል።

ከተሳታፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በወረዴው አስተዳዳሪ አቶ መስፍን በጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ልሳኑ አለማየሁና በሌሎች ባለድርሻ አካላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

በንቅናቄ  መድረክ ላይ  የማሻ ወረዳ ብልጽግና ፓርት ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ደመቀ ወልደየስን ጨምሮ የወረዳ አመራሮች የግብርና ጽ/ቤት ባለሙያዎች የቀበሌ  አስተዳዳሪዎችና በግብርና ስራ የተሻለ ተሞክሮና ሞዴል የሆኑትን አርሶ አደሮች ወጣቶችና ሴቶች ተሳትፏል።