January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በሸካ ዞን የኪ ወረዳ ”ከቃል ወደ ባህል” በሚል መሪ ቃል ለተከታታይ ሶስት ቀናት ስሰጥ የነበረው የአመራር መድረክ ተጠናቋል።

ከቃል ወደ ባህል በሚል መሪ ቃል ለአጠቃላይ አመራር ግምገማና ማጥራት ስራ ያስፈለገበት ዋነኛ ዓላማ አመራሩ የሀገርቱን ለውጥ የማስቀጠል ኃላፊነት ያለው በመሆኑ ትኩረት እንድሰጥበት ነው ተብሏል።

በመድረኩ ለሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የሚያዘጋጂና ተሻሽሎ በቀረበው የብልጽግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ ላይ መነሻ በማድረግ በጥልቀት ለአመራሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሀሳቦች ቀርበው ምክክር ተደርጎበታል።

የተመዘገቡ ድሎችን በማስቀጠል የሚታዩ ጉድለቶችን ትኩረት ሰጥቶ በማረም ጉድለቶን አመራሩ አምነውና ተቀብለው ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን በተገቢው እንዲያገለግሉ በመድረኩ ተገልጿል።

በስልጠናው ወቅት አስተያየት ሰጭዎች እንደገለፁት
ወቅቱን ጠብቆ መድረክ መፍጠር ብቻ ሳይሆን በሚሰራበት ጊዜ ራስን መገምገም እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

የሸካ ዞን  የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ አለሙ በመድረኩ ላይ  እንደተናገሩት ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ነገ ለማሻገር አመራሩ በመቀናጀትና በእቅድ እንዲሁም የአሰራር ስረዓቱን በቅንጂት መስራት ብልሹ አሰራርን መቅረፍ ፣ፍትህን በአግባቡ ማስከበር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ለተነሱ ሀሳቦችም የሚመለከታቸው አካላት ሚላሽና ማብራርያ በመስጠትመ መድረኩ ተጠናቋል።