በመላ ሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ በየ50 እና 120 ኪሎ ሜትር ርቀት እንዲቋቋም ተወሰነ።
በነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የኢነርጂ ዘርፍ ቁጥጥር ስራ አስፈጻሚ ባህሩ ኦልጅራ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደተናገሩት÷ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ሲስተም የቁጥጥር ማዕቀፍን የያዘ መመሪያ ከሰሞኑ ጸድቋል።
መመሪያው በዋናነት ፈቃድ አሰጣጥ፣ የቻርጅ አገልግሎት ታሪፍ፣ የሀይል አቅርቦት ደረጃ እና ደህንነትን መያዙን ተናግረዋል።
አሁን ላይም ሶስት አይነት ቻርጅ ማድረጊያ ቦታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ እነዚህም ሰዎች ከቤታቸው ቻርጅ ማድረግ የሚችሉበት፣ ተቋማት እና ድርጅቶች ደግሞ ለንግድ ላልሆነ አላማ በቁጥር ያልተገደቡ ተሽከርካሪዎቻቸውን ቻርጅ የሚያደርጉበት መሆኑን አንስተዋል።
በተጨማሪም የህዝብ ወይም ለንግድ ዓላማ ተብሎ የቻርጂንግ መሰረተ ልማት ገንብቶ የአገልግሎት ክፍያ የሚሰበሰብበት መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህም ለንግድ አላማ የሚቋቋሙት የቻርጂንግ ቦታዎች በፍጥነት መንገዶች ላይ በየ50 ኪሎ ሜትሩ ርቀት በሁለቱም መንገድ በኩል የሚገነቡ መሆናቸውን አቶ ባህሩ ኦልጅራ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ለከባድ ተሽከርካሪዎች እና አውቶቡሶች በዋና ዋና መንገዶች እና የፍጥነት መንገዶች ላይ በየ 120 ኪሎ ሜትሩ የቻርጅ ማድረጊያ ቦታ እንዲቋቋም ተወስኗል ብለዋል።
እስካሁን ድረስ ለቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ የቦታ ፈቃድ አለመሰጠቱን ገልጸው፤ ነገር ግን ከዚህ ቀደም የቻርጅ ማድረጊያ ያቋቋሙ አካላት መመሪያው ከጸደቀበት ጊዜ አንስቶ በ6 ወር ውስጥ ፈቃድ መውሰድ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
(ኤፍ ኤም ሲ)
More Stories
በጤና ተቋማት የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በመከላከልና ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ትኩረት ማድረግ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ይጠበቃል ተባለ ።
ኢትዮጵያ በክህሎት ልማት ሁለተኛውን የዓርበኝነት ምዕራፍ ጀምራለች – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ላለው ፈጣን እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው፦ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር)