January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ፑቲን በሩሲያ አየር ክልል ውስጥ ስለተከሰከሰው የአዘርባጃን አውሮፕላን ይቅርታ ጠየቁ

ማሻ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2017 (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአገሪቱ አየር ክልል ውስጥ የተከሰከሰው የአዘርባጃን አውሮፕላን ላይ ለደረሰው አሰቃቂ አደጋ ይቅርታ ጠየቁ።

የሀገሪቱን ፕሬዚዳንት ኢልሃም አሊዬቭን ይቅርታ የጠየቁት ፑቲን “አሳዛኝ ክስተት” ያሉት የአውሮፕላን መከስከስ በመፈጠሩ እና በአደጋው ምክንያት ለጠፋው የሰው ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎችም በቶሎ እንዲያገግሙ ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ክሬምሊን ባወጣው መግለጫ በአካባቢው ጥቃት በመፈጸም ላይ የነበሩ የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ላይ የሩሲያ አየር መከላከያ ጥቃቱን የመከላከል ስራ አየሰራ እንደነበር መግለጹን አሶሼትድ ፕሬስ በዘገባው አስነብቧል፡፡

ይሁን እንጂ የአዘርባጃኑ አውሮፕላን በስህተት በሩሲያ የአየር መከላከያ ኃይል ተመትቶ ይሁን አይሁን ተገለጸ ነገር የለም።

62 መንገደኞችንና አምስት ሠራተኞችን ያሳፈረ የአዘርባጃን አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን በካዛኪስታን አክታው ከተማ አቅራቢያ ባሳለፍነው ረቡዕ ተከስክሶ የ38 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

ምንጭ ከኤፍ ኤም ሲ ነው