February 2, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በከተማው የአስፓልመንት የመንገድ ስራ ከዳር እንድደርስ ሁሉም የበኩላቸውን እንዲወጡ የማሻ ከተማ አስተዳደር ጥሪ አቀረበ

ከተማ አስተዳደሩ ከማሻ 30 አስከ ማድያ ደረስ ካሉት የከተማ ነዋሪዎች ጋር በከተማው አሰፓልት መንገድ ስራ ዙርያ የውይይት መድረክ አካሂደዋል።

በመድረኩም ላይ የተገኙት የማሻ ከተማ ከንቲባ አቶ ሠራዊት አየነው እንደገለፁት መንግሥት የከተሞችን እድገት ለማሳለጥ ከፍተኛ ጥሬት እያደረገ ባለበት ወቅት የማሻ ከተማን እንደ ሌሎቹ ከተሞች ለማሳደግ ህብረተሰቡ ከመንግሥት ጎን ሆኖ እንድደግፍ ገልፀዋል።

በማሻ ከተማ የሚጀምረውን አስፓልት መንገድ ለከተማው እድገት ይበልጥ እንድሳለጥ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ያነሱት አቶ ሠራዊት ለዚህም ስራ ስኬት የከተማ ነዋሪዎች ድርሻ የጎላ ልሆን ይገባል ብለዋል።

ይህ ስራ ውጤታማ እንድሆን ከከተማ ነዋሪዎችና በበየደረጃው ከሚገኙ አካላት ጋር በመተማመን ስራ እንድጀመር መደረጉን ተናግረዋል።

የማሻ ከተማ የመንግሥት ዋና ተጠር አቶ መልካሙ እንዳሻው በበኩላቸው ያለህብረተሰብ ተሳትፎ የከተማውን እድገት ማረጋገጥ እንደማይቻል ገልፀው ለዝህም ተቀናጀቶ መስራት ቀዳም ተግባር ልሆን ይገባል ብለዋል ።

የውይይቱ ተሳታፍዎች በበኩላቸው መመሪያውና ደንቡ በሚለው መሠረት የንብረታቸው ካሣ እንድከፈልላቸው በመጠየቅ ለከተማዋ ሁለንተናዊ እድገት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ገልፀዋል።