January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ በአዲሱ ሪፎርም ዕሳቤዎችና በአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ለዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች በቦንጋ ከተማ ስልጠና ሰጠ።

የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ እንዳሻዉ በመክፍቻ ንግግራቸው እንደገለጹት አዲሱን ሪፎርም መሰረት ባደረገ መልኩ በአንድ ማዕከል ለህብረተሰቡ አገልግሎት በመስጠት እና የአሰራር ስርዓቱን በማሻሻል ከወቅቱ እሳቤ ጋር በማስተሳሰር የተሻለ ዉጤት ማስመዝገብ አለብን ብለዋል።

የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሰለሞን አየለ በበኩላቸዉ የተቋማት ግንባታ ለስራ ፈላጊዎችና ኢንተርፕራይዞች የሚሰጡ ህጋዊነትን የማስፈን እና የመንግስታዊ ድጋፍ አገልግሎቶችን በተቀናጀ መልኩ ከአንድ ስፍራ በአንድ አስተባባሪነት ዜጎች አገልግሎት ማግኘት ያስችላል ብለዋል