ማሻ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2017 (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) የሩሲያ ኑክሌር፣ ራዲዬሽንና ኬሚካል ጥበቃ ኃይል ዋና ኃላፊ ሌተናንት ጀነራል ኢጎር ኪሪሎቭ እና እረዳታቸው በተጠመደ ፈንጂ ምክንያት ሞስኮ ውስጥ ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል፡፡
ኃላፊው እና እረዳታቸው ሕይወታቸው ያለፈው ሞስኮ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ በስኩተር ላይ በተጠመደ ፈንጂ መሆኑን የሀገሪቱ መርማሪ ኮሚቴ አስታውቋል።
300 ግራም የሚመዝነው ፈንጂ በርቀት መቆጣጠሪያ አማካኝነት መፈንዳቱን ዩሮኒውስ ዘግቧል፡፡
ሌተናንት ጄነራሉ የተከለከለ ኬሚካል በዩክሬን ጦርነት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቅደዋል በሚል ዩክሬን ትናንት መክሰሷ ይታወሳል፡
More Stories
የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ የሚፈቅድ አዋጅ ጸደቀ
በማሻ ወረዳ ጋቲሞ ቀበሌ ትምህርት ቤት ግቢ በ1 ሄክታር መሬት ላይ የለማው የበጋ መስኖ ስንዴ ከ200,000 ሺህ ብር በላይ ገቢ ማስገኘቱን ተገለፁ።
shekki-noone geto