የሶሪያ አማጺያን በኤችቲኤስ እየተመሩ 24 አመታት ያስቆጠረውን የአላሳድን አገዛዝ ለአንድ ሳምንት በዘለቀ መብረቃዊ ጥቃት መገርስስ ችለዋልአሜሪካ በሽር አላሳድን ካስወገዱት አማጺ ቡድኖች ጋር የመነጋገር ፍላጎት አለኝ አለች።አሜሪካ ፕሬዝደንት በሽር አላሳድን ካስወገዱት የሶሪያ አማጺ ቡድኖች ጋር መነጋገር እንደምትፈልግ እና በቀጣናው እንደ ቱርክ ያሉ አጋሮቿ መደበኛ ያልሆነ ዲፕሎማሲያዊ ንግግር እንዲያመቻቹላት መጠየቋን ሮይተርስ ዘግቧል።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር ዋሽንግተን በሽብር የፈረጀችውን ጨምሮ ከብዙ ቡድኖች ጋር መነጋገር ትፈልጋለች ብለዋል።”ባለፉት ቀናት ይህን ለማድረግ እየተንቀሳቀስን ነው። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ራሳቸው ሶሪያ ውስጥ ተጽዕኖ ካላቸው ሀገራት ጋር ተነጋግረዋል፤ ይህን እንቀጥልበታለን” ብለዋል ሚለር።በቀጣናው ያሉ መንግስታት እንዲሁም ምዕራቡ አለም ቀደም ሲል ከአልቃ ኪዳ ግንኙነት ከነበረው እና በአሜሪካ፣ በአውሮፓ ህብረት፣ በቱርክ እና በመተድ በሽብር ከተፈረጀው ሀያት ታህሪር አል ሻም(ኤችቲኤስ) ጋር ግንኙነት ለመፍጠር እየተሯሯጡ ናቸው።የሶሪያ አማጺያን በኤችቲኤስ እየተመሩ 24 አመታት ያስቆጠረውን የአላሳድን አገዛዝ ለአንድ ሳምንት በዘለቀ መብረቃዊ ጥቃት መገርስስ ችለዋል።ሚለር እንዳሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከቀጣናው መሪዎች ጋር ማውራታቸውን እና በላፉት አራት ቀናት ውስጥ ለሁለት ጊዜ ከቱርኩ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳን ጋር አውርተዋል።ቱርክ በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ወታደሮች ያሏት ሲሆን ለተወሰኑ አማጺ ቡድኖችም ድጋፍ ትሰጣለች።አሜሪካ ከኤችቲኤስ መሪ አህመድ አል ሻራ ወይም አቡ መሀመድ አል ጎላኒ ጋር መነጋገር ትፈልግ እንደሆነ የተጠየቁት ቃል አቀባዩ መልስ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም፤ ነገርግን አያስፈልግምም አላሉም።”በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መነጋገር እንደምንችል እናምናለን” ብለዋል ሚለር።አሜሪካ የአሳድን አገዛዝ እንዲያስወግድ እና በሶሪያ የሸሪዓ ህግ እንዲያቋቁም በኢራቁ አልቃ ኢዳ ኃላፊነት ሰጥቶታል በሚል ነበር ጎላኒን በ2013 በሽብር የፈረጀችው።ያልተጠበቀው የአሳድ አገዛዝ ውድቀት ኢራን እና ሩሲያ በአረቡ አለም ተጽዕኖ ለመፍጠር ይጠቀሙበት የነበረውን ምሸግም አሳጥቷቸዋል ተብሏል። አሳድ ከ13 አመታት የእርስበርስ ጦርነት በኋላ አማጺያን ደማስቆን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ወደ ሩሲያ መኮብለሉ ተገልጿል።የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የአሳድን ውድቀት ለአስርት አመታት በጭቆና ውስጥ ለነበሩ ሶሪያውያን ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ሲሉ ገልጸውታል። ነገርግን ሀገሪቱ አደጋ እና አለመረጋጋት ሊያጋጥማት ይችላል የሚል ማስጠንቀቂያ አክለዋል።የሶሪያ ጦርነት ባለበት የቆመ ይመስል ስለነበረ በባይደን ስር ያለው የአሜሪካ አስተዳደር ባለፉት ከአራት አመታት ውስጥ ዋና ትኩረቱን ለጋዛ እና ዩክሬን አይነት ጦርነቶች ነበር።
Al-Ain
More Stories
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን ጋር የሚያደርጉት ንግግር እየተመቻቸ መሆኑን ገለጹ።
የአሜሪካ ኮንግረስ በአለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ድምጽ ሰጠ
አስደንጋጩ የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት አልበረደም