January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የዞኑን ህዝብ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ሽፋን ወደ 45 % ለማድርስ አቅዶ 42% ማከናወን መቻሉን የሸካ ዞን ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ አሳወቀ።

የሸካ ዞን ውሃ ማዕድን ና ኢነርጂ መምሪያ 2016 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀምና የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀምን አሰመልክቶ የምክክር መድረክ በማሻ ከተማ ተካሂደዋል።በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ በላቸው ጋራ እንደገለፁት የዞኑን የንፁ መጠጥ ውሃ ሺፋን ከነበርበት 37 .5 ፐርሰንት ወደ 45 መቶ ለማድረስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።ለስራ አፈጻጸም እንደችግርና ክፍተት ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከሚመለከታቸው አካላቶች ምላሾችና ማብራሪያዎች ተሰጥቶባቸዋል።

ዘጋቢ ትዕግስት በዛብህ