January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ከኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዮሪ ሙሴቬኒ ጋር በመሆን ኢትዮጰያ እና ሶማሊያ የአፍሪካ ቀንድን ወደ አለመጋጋት ውስጥ ሊከት የሚችለውን ችግር በውይይት እንዲፈቱ ጥረት እንደሚያደርጉ በትናንትናው እለት መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ሶማሊያ ውስጥ አልሸባብን እየተዋጉ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ያላት ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ ባለፈው የፈረንጆቹ አዲስ አመት ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር ወደብ ለመገንባት የተፈራረመችው ስምምነት ሞቃዲሹን አስቆጥቷል።ሶማሊላንድ ለኢትዮጵያ 20 ኪሎሜትር የሚረዝም የባህር ጠረፍ በ50 አመት የሊዝ ኪራይ ለመስጠት የተስማማችው፣ ኢትዮጵያ በምላሹ የሀገርነት እውቅና እንድትሰጣት በመፈለግ ነበር።ሶማሊላንድ በምርጫ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የምታደርግ እና ነጻነቷን ካወጀችበት ከ1991 ጀምሮ በአንጻራዊነት ሰላማዊ እና የተረጋጋች ብትሆንም አለምአቀፋዊ የሀገርነት እውቅና ማግኘት አልቻለችም::

al-ain