
የሬሚዲያል ፈተና ከሰኔ ወር መጀመሪያ ጀምሮ ይሰጣልየሬሚዲያል ፈተና ከሰኔ ወር መጀመሪያ እስከ 15 ባሉት ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተማሪዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ አቶ በየነ ተዘራ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የዘንድሮውን የሬሚዲያል ፈተና ከሰኔ ወር መጀመሪያ እስከ 15 ባሉት ቀናት በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ለመስጠት እየተሠራ ነው፡፡ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ ፈተናውን በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ ነው ያሉት አቶ በየነ፤ ፈተናው በኦንላይን፣ በኦንላይንና በወረቀት አልያም በጥብቅ ቁጥጥር በወረቀት ለመስጠት ታቅዶ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡ባለፈው ዓመት ከነበሩ ክፍተቶች ትምህርት በመውሰድ ዘንድሮ ፈተናው በጥብቅ ቁጥጥር በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን በመግለጽ፤ ፈተናው በማዕከል ደረጃ በጥብቅ ቁጥጥር እንደሚከናወን ተመላክቷል።
ምንጭ : ኢ.ፕ.ድ
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ