የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አየር መንገድን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ እንደሚያስገባ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ገለጹ።ዋና ስራ አስፈጻሚው ለኢዜአ እንደገለጹት፥ አየር መንገዱ በራዕዩ መሰረት ሊደርስበት ያቀደው ደረጃ ላይ ለመድረስ በሁሉም አቅጣጫ በፈጣን የእድገት መንገድ ላይ ይገኛል።በተለይ የአፍሪካ አየር መንገዶችን በማቋቋም ረገድ አየር መንገዱ ሰፊ ተሞክሮ እንዳለውና በቅርቡም በኮንጎ ኪንሻሳ አዲስ አየር መንገድ ለማቋቋም ከሀገሪቱ መንግስት ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን ገልጸዋል።
የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አየር መንገድን በ1 ወር ውስጥ ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅት ተጠናቋል – አቶ መስፍን ጣሰው

More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ