December 3, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የአለም የማራቶን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበችው ሩት ቼፕንጌቲች የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የክብር እንግዳ ትሆናለች

ከሳምንታት በፊት በተካሄደው የቺካጎ ማራቶን የዓለማችን ፈጣኑን የማራቶን ሰዓት ያስመዘገበችው ኬንያዊቷ አትሌት ሩት ቼፕንጌቲች በአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ውድድር ላይ በክብር እንግድነት ለመታደም በሚቀጥለው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ ትገባለች። “ወደ ኢትዮጵያ ልመጣ በመሆኔ በጣም ደስ ብሎኛል” ስትል ሩት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር አዘጋጆች ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ ተናግራለች። “በእንግድነት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣቴ ክብር ይሰማኛል እናም ኃይሌን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ አትሌቶችን ለማግኘት ጓጉቻለሁ” ብላለች፡፡ ቼፕንጌቲች ባለፈው ወር በቺካጎ ሶስተኛ የማራቶን ሻምፒዮን በመሆን 2 ሰአት ከ9 ደቂቃ ከ56 ሰከንድ አዲስ የአለም ክብረወሰን አስመዝግባለች። በዚህም በኢትዮጵያዊቷ ትግስት አሰፋ ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን ከሁለት ደቂቃ በታች በማሻሻል አጠናቃለች።

EBC