January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት እና የደረሱ ውድመቶች በንጽጽር

በእስራኤል ከተገደሉ 42 ሺህ ፍልስጤማዊን መካከል ጨቅላ ህጻናትን ጨምሮ ፕሮፌሰሮች፣ ጋዜጠኞች እና ሐኪሞች ይገኙበታል

በእስራኤል በኩል 1 ሺህ 700 ገደማ ዜጎች በሐማስ ተገድለዋል ተብሏልአንድ ዓመት የሞላው የእስራኤል -ሐማስ ጦርነት እና የደረሰው ውድመትለፍልስጤም ነጻነት የሚታገለው ሐማስ በእራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ የተጀመረው ጦርነት አንድ ዓመት ሞልቶታል፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዚህ ጦርነት የደረሱ ጉዳቶችን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት በፍልስጤም በኩል 41 ሺህ 788 ንጹሃን ሲገደሉ በእስራኤል በኩል ደግሞ 1 ሺህ 677 ዜጎች ተገድለዋል፡፡እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በፍልስጤም በኩል ከተገደሉት አጠቃላይ ሟቾች ውስጥ 60 በመቶው ሴቶች እና ህጻናት ናቸው፡፡በጥቃቱ 885 ሐኪሞችን ጨምሮ 173 ጋዜጠኞች፣ 710 ጨቅላ ህጻናት ሲገደሉ 19 ሺህ ህጻናት ወላጅ አልባ ሆነዋልም ተብሏል፡፡ከዚህ በተጨማሪም 115 ተመራማሪዎች፣ የዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰሮች እና አጥኚዎችም በእስራኤል ተገድለዋል፡፡

Al-Ain