6ኛው ዙር የኢሬቻ ፎረም አባ ገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች፣ አምባሳደሮች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት፣ የፌደራል፣ ክልልና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ፎሌዎች፣ ዲያስፖራዎች እንዲሁም የከተማችን ነዋሪዎች በተገኙበት በዓድዋ ድል መታሰቢያ በድምቀት አካሂደናል።ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሃ ማንነቶች ባለ ፀጋ እንደመሆኗ መጠን ህዝባዊ እና ኃይማኖታዊ በዓላት አንድነትን፣ ፍቅርንና የህዝቦች ትብብርን በማፅናት ረገድ አይነተኛ ሚና የሚጫወት ሲሆን የኢሬቻ በዓል የሰላም፣ የእርቅ፣ የአንድነት፣ የአብሮነት እንዲሁም የወንድማማችነትና እህትማማችነት በዓል ሆኖ በመከበር ላይ ይገኛል።ኢሬቻ የገዳ ስርዓት አንዱ ምሰሶ ሲሆን የምስጋና፣ የሰላም እና የወንድማማችነት ተምሳሌት ሆኖ የኦሮሞ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ ከፈጣሪ፣ ከተፈጥሮ እና ከሰው ሁሉ ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያድስበት ነው። በኢሬቻ የተራራቀ ይቀራረባል፤ የተቀያየመም ይታረቃል።
Woreda to World
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።