October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት የዳኞች መደበኛ ስራ የማስጀመሪያ ውይይት መድረክ በማሻ ከተማ አካሂዷል።

መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት አቶ በላቸው ጀመሬ እንደተናገሩት መደበኛ ችሎቶች በማይኖሩበት ወቅት ከሰብአዊ መብቶችና የማይታለፉ ጉዳዮችን በሚመለከት ዳኞችን በመመደብ ወደ ስራዎች ለመግባት የመጀመሪያ ውይይትና ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል።የውይይት ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የአሰራር ስርዓትንና መመሪያን በመከተል ሁሉም ሚናውን በመለየት ስነ-ምግባር በመላበስና ባለፉት በጀት ዓመት ከተገልጋዩ ህዝብ የተሰጡ ሐሳቦችን ፈትሾ በአዲሱ በጀት ዓመት አገልግሎት መስጠት ይገባናል ብለዋል።

ዘጋቢ ካሳሁን ደንበሎ