October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ባህላዊ እሴቶችን ጠብቆ በማልማትና በመንከባከብ ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ የአሁኑ ትውልድ ትልቅ አደራ አለበት ያነጋገራቸው የህብረተሰብ ክፍሎች፦

ከ146 ዓመታት በኋላ የሸካቾ ባህላዊ የአስተዳደር መዋቅር ወደ ስራ ከገባ ጊዜ “ማሽቃሬ ባሮ”የዘመን መለወጫ በዓል በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ በድምቀት ተከብሯል። የሸካቾ ባህላዊ የአስተዳደር መዋቅር ለዘመናት ተረስቶ የቆየ ቢሆንም ተመልሶ ዳግም ወደ ስራ በመግባቱ በርካታ ተግባራት በመከናወናቸው በዞኑ ለውጦች መምጣት መቻሉና እነኝህንና የመሳሰሉትን ዕሴቶች በመጠበቅና በመንከባከብ ማስተላለፍ የሁሉም ድርሻ መሆኑን ነው ያሳሰቡት።ባህልን ማልማት፣መንከባከብ ፣መጠበቅ፣ የህዝቦች ትልቅ የማዕዘን ድንጋይ፣መነሻ ታሪካቸውን የሚያዩበት መነጽር፣ ዘላቂ ልማትና ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያስችል ወሳኝ እሴት በመሆኑ ማልማትና ማሳደግ ያስፈልጋል።