October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

እስራኤል በሊባኖስ በፈጸመችው የአየር ላይ ጥቃት ተጨማሪ የሂዝቦላህ ከፍተኛ አመራር መግደሏን አስታውቃለች፡፡

በሊባኖስ በመሸገው ሂዝቦላህ ላይ የሚወሰደው ሁለንተናዊ እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ገልጿል፡፡በዛሬው ዕለትም በቤሩት በተመረጡ የሂዝቦላህ ይዞታዎች ላይ የተሳካ የአየር ላይ ጥቃት መፈጸሙን ጦር ባወጣው መግለጫ አመላክቷል፡፡በዚህም የሂዝቦላህ ደህንነት ሃላፊና የማዕከላዊ ም/ቤቱ ወሳኝ አባል ነቢል ኳዑክ መገደሉን ነው ያስታወቀው፡፡ በአንጻሩ በከፍተኛ አመራሩ መገደል ዙሪያ ሂዝቦላህ ያለው ነገር አለመኖሩን ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡እስራኤል በሂዝቦላህ ላይ እየወሰደች ባለው ወታደራዊ እርምጃ የቡድኑን መሪ ሀሰን ነስራላህን ባሳለፍነው አርብ መግደሏ ይታወሳል፡፡