January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴርን የሪፎርም ስራዎች ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር)ና የገቢዎች ሚኒስትር አይናም ወይዘሮ ንጉሴ ተሳትፈዋል፡፡ጉብኝቱን አስመልክቶ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷”እንኳን ወደ ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በሰላም መጣቹሁ፤ የእረፍት ቀናቹሁን ሰውታቹሁ የተቋም ግንባታና የሪፎርም ስራዎቻችንን ስለጎበኛችሁ እጅግ እናመሰግናለን” ብለዋል።