October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ከአዳማ-ጂቡቲ የቁም እንስሳት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ይፋ ሆነከአዳማ ወደ ጂቡቲ የቁም እንስሳት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ይፋ መሆኑን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) አስታወቁ፡፡

ሥራአስፈጻሚው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ “ዛሬ ከአዳማ ወደ ጅቡቲ የመጀመሪያ የቁም እንስሳትን በባቡር ወደ ውጭ መላክ እንጀምራለን” ብለዋል፡፡የቁም እንስሳቱን በባቡር ወደ ውጭ ማጓጓዙ በእንስሳት ላይ ያለውን የትራንስፖርት ጫና በመቀነስ የኤክስፖርት ስጋ ጥራትን እንደሚሳድግ አመላክተዋል፡፡ይህም ኢትዮጵያ ለውጤታማ እና ዘላቂ ንግድ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው÷ ኢትዮጵያ በድንበር ላይ የሚደረጉ የካፒታል ፍሰቶችን ለማሳደግ ያላትን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አስረድተዋል(ኤፍ ቢ ሲ)