November 27, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ

የ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ሥራ መግባቱን ጥምር የፀጥታ ሃይሉ አስታውቋል፡፡ ጥምር የጸጥታ ሃይሉ በዓላቱ በድምቀት እንዲከበሩ ከሐይማኖቱ አባቶችና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ተናግረዋል፡፡ኮሚሽነር ጀነራሉ በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዳይጠናቀቅ ፍላጎት ያላቸው አካላትን ሴራ ለማክሸፍ ልዩ ልዩ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመው፤ የፀጥታ ሃይሉ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት መፈፀም በሚችልበት ቁመና ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በበኩላቸው÷ በዓሉ ሃይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር ጥምር የፀጥታ ሃይሉን በመደገፍ በኩል ህብረተሰቡ ትብብር እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ÷ በዓሉ ወደሚከበርበት ስፍራ ከበዓሉ አከባበር ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ነገሮች ይዞ መምጣት ክልክል መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ለፀጥታ ሃይሎች ሥራ ተባባሪ እንዲሆን ማገንዘባቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

EBC

You may have missed