October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ቱርክ የሶማሊያን የባህር ክልል ለመጠበቅ በቀጣዩ ወር የጦር መርከቦቿን ልትልክ ነው

ቱርክ በመዲናዋ አንካራ በ6 ሚሊየን ዶላር ለሶማሊያ ኤምባሲ ለመገንባት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኗ ተገልጿልቱርክ የሶማሊያን የባህር ክልል ከውጭ ከሚሰነዘር ስጋት ለመከላከል በመጪው ወር የጦር መርከቦቿን በአካባቢው ልታሰማራ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ በተያዘው የፈረንጆቹ አመት መጀመርያ የመከላከያ ስምምነትን የተፈራረሙት ሞቃዲሾ እና አንካራ በሁለትዮሽ እና የደህንነት ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ውሳኔ ላይ ደርሰዋል፡፡ ቱርክ በቀጣዩ ወር በሶማሊያ የባህር ክልል ታሰማረዋለች የተባለው የባህር ሀይልም የዚህ የመከላከያ ስምምነት አንድ አካል ነው፡፡ወደ ቀጠናው የሚመጡት ሁለት አይነት መርከቦች ሲሆኑ አንድኛው አንካራ በአካባቢው ለምታደርገው የነዳጅ ማውጣት እንቅስቃሴ የሚያግዝ ሲሆን ሌሎቹ ድግሞ የሶማሊያን የባህር ክልል እና የነዳጅ አውጭ ቡድኑን የሚጠብቁ ናቸው ተብሏል፡፡

Al-Ain