October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሩሲያ በትራምፕ ላይ የተኮሰው ግለሰብ ከዩክሬን ጋር ግንኙነት አለው መባሉ “በእሳት መጫወት” ዋጋ እንደሚያስከፍል የሚያሳይ ነው አለች

ዋሽንግተን የዩክሬን ኃይሎች ሩሲያን እንዲያሸንፉ በ10 ቢሊዮኖች የሚቆጠር ወታደራዊ ድጋፍ ለኪቭ አበርክታለችየሩሲያ ቤተመንግስት ክሬሚሊን የቀድሞውን የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕን ለመግደል ሞክራል የተባለው ግለሰብ ከዩክሬን ጋር ግንኙነት እንዳለው መጠርጠሩ “በእሳት መጫወት” ዋጋ እንደማያስከፍል የሚያሳይ ነው ብሏል። ክሬሚሊን በዚህ አስተያየቱ አሜሪካ ከሩሲያ ጋር እየተዋጋች ያለችውን ዩክሬይንን መደገፏ ተገቢ አለመሆኑን አመላክቷል።ዋሽንግተን የዩክሬን ኃይሎች ሩሲያን እንዲያሸንፉ በ10 ቢሊዮኖች የሚቆጠር ወታደራዊ ድጋፍ ለኪቭ አበርክታለች። የአሜሪካ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ(ኤፍቢአይ) በትራምፕ ላይ የተቃጣ የግድያ ሙከራ ነው ሲል ስለገለጸው የዛሬ ክስተት የተጠየቁት የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮፕ “ማሰብ ያለብን እኛ አይደለንም። መጨነቅ ያለበት የአሜሪካ የደህንነት አገልግሎት ነው። ያም ሆነ ይህ በእሳት መጫወት ዋጋ ያስከፍላል” ሲሉ ተናግረዋል።የግድያ ሙከራው አሜሪካን ወደ አለመረጋጋት ሊከታት ይችላል ወይ ተብለው የተጠየቁት ፔስኮቭ ሩሲያ ሁኔታውን እየተከታተለችው ቢሆንም ይህ ሩሲያን የሚስጨንቅ ጉዳይ አይደለም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።”በፖለቲካ ተፎካካሪዎች መካከል ያለውን ጨምሮ በእዚያ ያለው ውጥረት ከባድ እንደሆነ አይተናል” ብለዋል ፔስኮቭ። “የፖለቲካው ትግሉ እየጠነከረ ነው፤ ብዙ ዘዴዎችም ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው።”ግዙፎቹ የአሜሪካ ሚዲያዎች ሲኤንኤን፣ ፎክስ ኒውስ እና ኒው ዮርክ ታይምስ በስም ያልጠቀሱትን ምንጭ ጠቅሰው እንደዘገቡት የግድያ ሙከራ በማድረግ የተጠረጠረው ርያን ወስሌይ ሮውዝ የተባለ ከሀይቲ የመጣ የ58 አመት ግለሰብ ነው።የሮውዝ ስም የያዙ ሶስት የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገችው ባለው ጦርነት ጠንካራ የዩክሬይን ደጋፊ መሆኑን የሚያመለክቱ ናቸው ተብሏል።ኒው ዮርክ ታይምስ በ2023 ዩክሬንን ለመርዳት ፈቃደኛ ስለሆኑ አሜሪካውያን ለሰራው ጽሁፍ ሮውዝን ቃለ መጠይቅ እንዳደረገለት ገልጿል። ሮውዝ በወቅቱ ለኒው ዮርክ ታይምስ እንደተናገረው በ2022 ወደ ዩክሬን ሄዶ በርካታ ወራትን ማሳለፉን እና ከታሊባን የሸሹ የአፍጋን ወታደሮችን ዩክሬን ውስጥ ለመመልመል ሲሞክር ነበር። ትራምፕ የግድያ ሙከራ ሲደረግባቸው ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

Al-Ain