ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ ሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሥልጠና እየተሰጠ ነውOn Sep 14, 2024 359አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ ሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረና የአመራር አቅምን በሚገነቡ ወቅታዊ ጉዳየች ዙሪያ ስልጠና መሰጠት ጀምሯል፡፡ስልጠናውን የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) አስጀምረዋል።ስልጠናው “የሕልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተሰጠ የሚገኘው፡፡በመድረኩ በሀገሪቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን በላቀ ስኬት በመፈፀምና ተሞክሮን በማስፋት፣ ተግዳሮቶችን ወደ እድል በመቀየር የህዝብና የሀገርን ጥቅም ለማረጋገጥ በአመራሩ አቅም የሚያዝባቸው ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል።የብልፅግና ፓርቲ ከህዝቡ ጋር በመሆን በፈጸማቸው ተግባራት የተጎናፀፋቸውን አንፀባራቂ ድሎች ይበልጥ በማጎልበት በቀጣይ የሚያከናውናቸው የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ አቋምና ዝግጁነት እንደሚፈጠርበትም ተመላክቷል፡፡በጠንካራ ፓርቲ ጠንካራ የመንግስት አፈፃፀምን እውን በማድረግ ፓርቲው ለህዝብ የገባውን ቃል በተጨባጭ ለማሣካት ከፍተኛ አቅም የሚፈጥር ይሆናል መባሉንም የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡እስከ መስከረም 15 ቀን 2017 ዓ.ም በሚቆየው ስልጠና ከሀገሪቱ ሁሉም ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከፌዴራል ተቋማት የተውጣጡ ከ2 ሺህ በላይ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
FBC
More Stories
የቴፒ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የከተሞች ፕላን ኢኒስቲትዩት ተገለጸ፡፡
የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተመረጡ የግብርና፣ በቱሪዝም፣ በቴክኖሎጂ እና ማዕድን ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበየቻይናዋ ግዛት ከፍተኛ ልዑካን የተሳተፉበት የቻይና-አፍሪካ (ኢትዮጵያ) የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝም ና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በዓለም ለ45ኛ በኢትዮጵያ ለ37ኛ በክልሉ ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረዉ የዓለም የቱሪዝም ቀን ”ቱሪዝም ለሰላም” በሚል መር ቃል በቦንጋ ከተማ እየተከበረ ነዉ።