የኢትዮጵያ የሁልጊዜ ጥረት በጋራ ልማት ቀጣናዊ ትስስር መፍጠርና የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ገለጹ።አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ የልማትና የንግድ ግንኙነቷን በማጠናከር ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግና ለማምጣት እየሰራች ትገኛለች።በዲፕሎማሲው መስክም መልካም ግንኙነቶችን በማጠናከርና የሚደርሱ ጫናዎችን ጭምር በመቋቋም ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን እያስመዘገበች ነው ብለዋል።የኢትዮጵያ መሰረታዊ ጥቅሞች የዛሬን መሻትና የወደፊት ፍላጎቶችን መሰረት ያደረጉ ስለመሆኑም አብራርተዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ጥረት በጋራ ልማት ቀጣናዊ ትስስር መፍጠርና የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በመሆኑ በዚህ ረገድ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ የሚፈጠሩ ልዩነቶችን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ፣ በሰጥቶ መቀበል መርህ ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑንም አረጋግጠዋል።የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ እንዳይሳለጥ ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትም የመንግሥት ጥረት የቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል።ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትና እድገት ዋነኛው መሰረት ሰላም መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደር ታዬ፤ ለዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ሁለንተናዊ እድገት መረጋገጥ በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
EBC
More Stories
በ2016 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የ8 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል- ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)
ሙስና የተበላሸ አስተሳሰብ፣ ባህልና አሰራር ውጤት ነው – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ
የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት የዳኞች መደበኛ ስራ የማስጀመሪያ ውይይት መድረክ በማሻ ከተማ አካሂዷል።